ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ክንፍ ላይ የምህንድስና ማሻሻያ ማድረጉ ዛሬ ይፋ ተደረገ።
የአውሮፕላን ጥገና ባለሙያዎች በአፍሪካ አቪየሽን ታሪክ የመጀመሪያ ሊባል የሚችል /winglet modification/ ማድረጋቸው ተሰምቷል።
ማሻሻያው የተደረገው አየር መንገዱ በሚያበራቸው የቦይንግ 767 አውሮፕላኖች ላይ ሲሆን፤ ይህም በዓመት እስከ 500 ሺኅ ጋሎን ነዳጅ እንዲቆጥብ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደርጋል ነው የተባለው።
ማሻሻያው 277 ሺኅ ሜትሪክ ቶን የካርበን ልቀትንም የሚያስቀር ከመሆኑ ጋር ተያዮዞ፤ አየር መንገዱ በአካባቢ ጥበቃ የሚያደርገውን ጥረት የሚያግዝ ነው ሲል የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል።