ቻይና ለሦስተኛ ጊዜ የኮሮና መከላከያ ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ አበረከተች

ቻይና ለሦስተኛ ጊዜ የኮሮና መከላከያ ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ አበረከተች

A coronavirus diagnostic test kit sits displayed in this arranged photo at the TIB Molbiol Syntheselabor GmbH production facility in Berlin, Germany, on Thursday, March 6, 2020. TIB has reoriented its business toward coronavirus, running its machines through the night and on weekends to make the kits, which sell for about ???160 ($180) apiece. Photographer: Krisztian Bocsi/Bloomberg

ኢትዮጵያ ነገ ዜና የቻይና መንግሥት ለ3ኛ ዙር የኮሮና መከላከያ የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ለኢትዮጵያ መለገሱ ተሰምቷል።

አሁን ላይ በተደረገው ድጋፍ 500 ሺኅ ሰርጂካል የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል፣ 65 ሺኅ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል፣ 10 ሺኅ የሜዲካል አልባሳት እና የጫማ መሸፈኛ እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰርጂካል ጓንቶች የተካተቱበት እንደሆነ መረጃው ያሳያል።
የቻይና መንግሥት ኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል በምታደርገው ዘርፈ ብዙ ጥረት ድጋፉ እንዳልተለየ እና ወረርሽኙ ወደ አገሪቱ ከገባበት ከመጋቢት ወር ጀምሮ የሚያደርገው ድጋፍ ሳይቋረጥ መቀጠሉን የቻይና ኤምባሲ ገልጿል።
ቀሚያዝያ ወር ከቻይና የመጡ የሕክምና ቡድን አባላት ለ15 ቀናት በኢትዮጵያ የሕክምና ድጋፍ ሰጥተው ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው አይዘነጋም።

LEAVE A REPLY