ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል እና የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሁለት ሐኪሞችና 20 ተለማማጅ ሐኪሞች ወይም ኢንተርኖችበኮሮናቫይረስ መያዛቸው ታወቀ።
በተገኘው መረጃ መሠረት እስከ ማክሰኞ 17፣ ረቡዕ አራት እና ሐሙስ ደግሞ አንድ፤ በአጠቃላይ 22 ሐኪሞች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ ከእነዚህ መካከል ሠባቱ ሴቶች መሆናቸው ተሰምቷል።
የሕክምና ባለሙያዎቹ በቫይረሱ መያዛቸውን ተከትሎ ሁሉም ተለማማጅ ሐኪሞች ሥራ እንዳይገቡ እንደተነገራቸው፣ ከትናንት (ሐሙስ) ጀምሮ ሥራ አለመግባታቸውን ስሙን መግለጽ ያልፈለገ አንድ ተለማማጅ ሐኪም ለቢቢሲ በሰጠው አስተያየት ላይ ገልጿል።
ወደ ሆስፒታሉ የሚመጡ ታካሚዎች በቅድሚያ ከእነርሱ ጋር የሚገናኙ በመሆኑና በእነርሱ ከታዩ በኋላ ወደ ሌሎች ምርመራዎች እንዲላኩ የሚያደርገው ይህ የሥራቸው ሁኔታ ሳይሆን እንዳልቀረ በቫይረሱ ስለተያዙበት ምክንያት ሐኪሞቹ ቅድመ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
ተለማማጅ ሐኪሞቹ ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ አስፈላጊ የመከላከያ አልባሳትና ሌሎች አቅርቦት በበቂ ሁኔታ አለመቅረባቸው ተጋላጭነታቸውን ከፍ እንዳደረገውም ይናገራሉ።
“ሰርጂካል ማስክ እና አልኮል ተሰጥቶናል፤ በ15 ቀናት ዐስር የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ነው የሚሰጠን። አንድ ጭምብልን በአማካይ ከ24 ሰዓታት በላይ ነው የምንጠቀምበት” ያለው ተለማማጅ ሐኪም፤ የመከላከያ ቁሶች በሆስፒታሉ ውስጥ በበቂ ሁኔታ እንደሌሉም ይፋ አድርጓል።
በኮቪድ 19 ቫይረስ ከተያዙት ሴት ተለማማጅ ሐኪሞች መካከል አንዷ እርሷን ጨምሮ 22 ተለማማጅ ሐኪሞች በቫይረሱ መያዛቸውን ጠቁማ፤ በበሽታው የተያዘችበትን ምክንያት ወይም አጋጣሚ ግን በውል እንደማታውቀው ገልጻለች።
ተለማማጅ ሐኪሟ በሆስፒታሉ ውስጥ የእጅ ጓንትና ሌሎች ከቫይረሱ የመከላከያ ግብዓቶች እጥረት መኖሩን ተናግራ፤
“ብዙ ጊዜ በባዶ እጅ ነው የምንሰራው። በአብዛኛው ታማሚዎች የእጅ ጓንት እንዲገዙ እናደርጋለን። መግዛት የማይችሉትን ግን በባዶ እጃችን ሥንሰራ ከርመናል” ስትል የችግሩን ጥልቀት ለማሳየት ሞክራለች።