በአሰሪዎቻቸው ጥቃት የደረሰባቸውና መጠለያ ያጡ 165 ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ ተመለሱ

በአሰሪዎቻቸው ጥቃት የደረሰባቸውና መጠለያ ያጡ 165 ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ ተመለሱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በቤይሩት ሊባኖስ በአሰሪዎች በደልና የመብት ጥሰቶች፣ የአካልና የስነ-ልቦና ጉዳት የደረሰባቸው፣ መጠለያና ምግብ አጥተው የነበሩ 165 ኢትዮጵያውያን ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ታወቀ።

ሊባኖስ የሚገኘው ቆንስላ ጀነራል ጽሕፈት ቤት ከኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ማኅበር እና ከሌሎች ድጋፍ ከሚያደርጉ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ግለሰቦች ጋር በመተባበር የጉዞ ሰነዶቻቸውንና ሌሎች ጉዳዮችን በመጨረስ ስደተኞቹ ትናንት ማታ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ተደርጓል ብሏል።
በቤይሩት በአሰሪዎች በደልና የመብት ጥሰቶች፣ የአካልና የስነ-ልቦና ጉዳት የደረሰባቸው እንዲሁም መጠለያና ምግብ አጥተው የነበሩ 165 ዜጎችን፤ ኮሙኒቲ ማኅበሩና ሌሎች አካላት የአውሮፕላን ቲኬቶችን ወጪዎችን ከመሸፈን ባሻገር፣  ሌሎችም እገዛዎችን በማድረግ ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ላደረጉት ትብብር ቆንስላ ጽህፈት ቤቱ ምስጋና ይድረሳቸው ብሏል።
157 ዜጎች በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ማኅበር መጠለያ ውስጥ የሚገኙ በመሆኑ እነዚህን ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ቆንስላ ጀነራል ጽሕፈት ቤቱ የጉዞ ሰነዳቸውን እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ለማስጨረስ እየሠራ መሆኑ ተነግሯል።
በተያያዘ ዜና 75 ኢትዮጵያውያን በ8ኛ ዙር የትራንስፖርት ወጪያቸውን በራሳቸው በመሸፈን ወደ ሃገር ቤት ለመጓዝ ተመዝግበው የነበሩ የመኖሪያ ፍቃድ ያልነበራቸው ዜጎቻችን የጉዞ ሰነድና የመውጫ ቪዛ የተሰራላቸው ከመሆኑ ባሻገር፤ ምርመራ በማጠናቀቃቸው ቲኬቶቻቸውን ራሳቸው በመግዛት ዛሬ ማታ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ ተነግሯል።

LEAVE A REPLY