በያዝነው ሳምንት 400 ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገር ቤት መመለሳቸውን በቤይሩት የሚገኘው ቆንስላ ገለጸ

በያዝነው ሳምንት 400 ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገር ቤት መመለሳቸውን በቤይሩት የሚገኘው ቆንስላ ገለጸ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና በዚህ ሳምንት 400 ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገር ቤት መመለሳቸውን በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀነራል ጽሕፈት አስታወቀ።

በሳምንቱ ወደ አገራቸው ከተመለሱት መካከል በእስር ቤት የነበሩ 18 እና የመኖሪያ ፈቃድም ሆነ ሌሎች ህጋዊ ሰነዶች ያልነበሯቸው በድምሩ 234 ዜጎች ይገኙበታል ነው የተባለው።
በአሠሪዎቻቸው የተለያዩ በደሎች ተፈፅሞባቸው እርዳታ ሲደረግላቸው የነበሩ 165 ዜጎችም ከተመላሾች መካከል የተካተቱ ሲሆን፤ ባለፉት ቀናት በተለያዩ ሰበቦች መነሻነት በረራ ያመለጣቸው 14 ዜጎች መኖራቸውን የጠቀሰው ቆንስላ ጽሕፈት ቤቱ በቀጣዮቹ ቀናት ወደ ሃገር ቤት እንዲመለሱ እየሠራሁ ነው ሲል ገልጿል።
በቀጣዩ 9ኛ ዙርም ከ3ሺኅ 500 በላይ ዜጎችን ለመመለስ ማቀዱን የጠቆመው ቆንስላ ጀነራል ጽ/ቤቱ ፤ በተጨማሪም በአሠሪዎቻቸው በደልና የመብት ጥሰት የደረሰባቸው 157 ኢትዮጵያውያንን ለመመለስ ጥረት ላይ መሆኑን እገኛለሁ ብሏል።
በሊባኖስ  የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀነራል ጽ/ቤት እነዚህን ዜጎች ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ከኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማኅበር፣ ከእምነት ተቋማት፣ ከእርዳታ ድርጅቶች እንዲሁም በሊባኖስና በሌሎችም አገራት ከሚገኙ ምግባረ ሰናይ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመተባበር እየተሠራ እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

LEAVE A REPLY