ፌደሬሽን ምክር ቤት ለቅዳሜ ነሐሴ 30 አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱ ታወቀ

ፌደሬሽን ምክር ቤት ለቅዳሜ ነሐሴ 30 አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱ ታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ለጊዜው የስብሰባው አጀንዳ ምን እንደሆነ ግን ምክር ቤቱ ባይገለጽም፤ ምክር ቤቱ በፌቡክ ገጽ ካሰራጨው ጥሪ ግን ቅዳሜ አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚደረግ ይፋ አድርጓል።

ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ቅርበት ያላቸው የዜና ምንጮች እንደገለጹት ከሆነ የፊታችን ረቡዕ ጳጉሜ 4 ቀን 2012 ዓ.ም ህወሓት በትግራይ አካሂደዋለሁ እያለው ስለሚገኘው ክልላዊ ምርጫ ላይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ታስቦ መሆኑ ይነገራል።
የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ሁለቱ ምክር ቤቶች (የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ም/ቤት) ቀጣዮ ሀገራዊም ሆነ ክልላዊ ሞርጫ እንዲራዘም ቢወስኑም ህወሓት አሻፈረኝ በማለት ምርጫ ለማካሄድ ምዝገባ መጀመሩን ተከትሎ የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ የቅዳሜውን አስቸኳይ ስብሰባ ለመጥራት እንደወሰነ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

LEAVE A REPLY