በደቡብ ኦሞ 19 ደሴቶች ይኖሩ የነበሩ 43 ሺኅ ሰዎች በጎርፍ አደጋ መኖሪያቸውን...

በደቡብ ኦሞ 19 ደሴቶች ይኖሩ የነበሩ 43 ሺኅ ሰዎች በጎርፍ አደጋ መኖሪያቸውን ለቀቁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ምክንያት እስከ ዛሬ ድረስ 43 ሺኅ 670 ሰዎች ከቀዬአቸው እንደተፈናቀሉ ተሰማ።

የደቡብ ክልል ኀብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር፣ እንዳሻው ሽብሩ  በወረዳው ላይ 62 ሺኅ ነዋሪ መኖሩን ጠቁመው በዳስነች ወረዳ የደረሰውን የጎርፍ አደጋ ተከትሎ ሦስት አራተኛው ነዋሪ ለመፈናቀል መገደዱን አረጋግጠዋል።
በደቡብ ኦሞ ዞን በዳሰነች ወረዳ ከሐምሌ 25፣ 2012 ዓ.ም ጀምሮ የተከሰተው የኦሞ ወንዝ መሙላት ያስከተለው ጎርፍን ተከትሎ በውሃ የተከበቡ 19 ደሴቶች ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ሰዎችን ለማውጣት በሞተርና ጀልባ የታገዘ ጥረት በማድረግ 43 ሺኅ 670 ቤተሰቦችን ማውጣትና በ8 ደረቃማ አካባቢዎች ማስፈር መቻሉን ሓላፊው ለቢቢሲ ገልጸዋል።
በክልሉ በስልጤ ዞን እንዲሁም ደቡብ ኦሞ ዳሰነች ወረዳ ላይ ጎርፍ ተከስቶ ሰዎች መፈናቀላቸውን የተናገሩት አስተዳዳሪው፤ ወደፊት ዝናቡ እየጠነከረ ሲመጣ ስጋት ካለባቸው የደቡብ ኦሞ አካባቢዎች መካከል ናፀማይ፣ ኛንጋቶም ፣ እና ሀመር ግንባር ቀደሞቹ ናቸው ብለዋል።
በዳሰነች ወረዳ የተፈናቀሉት ሰዎች በመጠለያ ውስጥ እንደሚገኙ እና ወደ ስድስት ሺኅ ሰዎች ይኖሩበት ከነበረው ሃይቅ ደሴት ላይ እንዲወጡ መደረጉም ታውቋል።
አስቀድሞ በወረዳው የኮሌራ ወረርሽኝ ይከሰታል የሚል ስጋት የነበረ ቢሆንም፤ እስካሁን ግን በጎርፍ ምክንያት በኮሌራ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ስድስት ብቻ እንደሆኑ ተሰምቷል።

LEAVE A REPLY