ሥድሥት የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ለኢትዮጵያ የሚደረገው ድጋፍ መቀነሱን በይፋ ተቃወሙ

ሥድሥት የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ለኢትዮጵያ የሚደረገው ድጋፍ መቀነሱን በይፋ ተቃወሙ

The Irrigation Ministers of Egypt, Ethiopia, and Sudan take part in a meeting to resume negotiations on the Grand Ethiopian Renaissance Dam, in the Sudanese capital Khartoum on December 21, 2019. - Egypt, Ethiopia and Sudan set last month in Washington a January 15 target for resolving the dispute over the construction by Addis Ababa of the Grand Ethiopian Renaissance Dam on the Nile. The Nile is a lifeline supplying both water and electricity to the 10 countries it traverses. Analysts fear the three Nile basin countries could be drawn into a conflict if the dispute is not resolved before the dam begins operating. (Photo by ASHRAF SHAZLY / AFP) (Photo by ASHRAF SHAZLY/AFP via Getty Images)

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ሥድሥት የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምታደርገው ድጋፍ እንዲቀነስ መደረጉን በመቃወም፤ ለአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ እና ለግምጃ ቤት ሓላፊው ስቲቭ ሙንሽን ደብዳቤ መጻፋቸውን ገለጹ።

አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምታደርገው ድጋፍ እንዲቀነስ መደረጉ እጅጉ አሳስቦናል ሲሉ ደብዳቤ የጻፉት የኮንግረስ አባላቱ፤
“ይህ የውጪ ድጋፍ እንዲቀነስ መደረጉ ታማኝ ከሆነች አጋራችን ጋር ያለንን ግንኙነት ከማሻከሩም በተጨማሪ፣ አሜሪካ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ በኢትዮጵያ፣ በግብጽ እና በሱዳን መካከል በሚደረገው ድርድር ላይ የሚኖራትን ተሳትፎና ገለልተኝነትን ጥያቄ ውስጥ ይጥላል” ሲሉም ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
ከዚህ በፊት የሲ አይ ኤ ሓላፊ ለነበሩት የአሁኑ የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ ደብዳቤውን የጻፉት የኮንግረስ አባላት ጄሰን ክሮው፣ ኢልሃን ኦማር፣ ኮኒን አልሬድ፣ ጆህን ግራሜንዲ፣ ጆይስ ቤቲ እና ጄራልድ ኮንሊይ  የተሰኙት ሰዎች መሆናቸውም ታውቋል።
ኢትዮጵያ ግንባታውን በማካሄድ ላይ ባለችውና ከሱዳንና ከግብጽ ጋር የሚደረገው ድርድር መቋጫ ባላገኘው የህዳሴ ግድብ ግንባታ ምክንያት ፤ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ለመስጠት አቅዳ የነበረውን ወደ 130 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የእርዳታ ገንዘብ ልትከለክል መሆኑ በስፋት መዘገብ ከጀመረ ሰንበትበት ማለቱ አይዘነጋም።
በቅርቡ ጉዳዮን አስመልክተው ምላሽ የሰጡት በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ፍጹም አረጋ፤ ከአሜሪካ ባለሥልጣናት በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ጠይቀው ባገኙት ማብራሪያ ለኢትዮጵያ ሊሰጥ ከታቀደው የገንዘብ ድጋፍ የታገደው በጊዜያዊነት ነው ማለታቸው ይታወሳል።

LEAVE A REPLY