ባይቶና በምርጫው የተሰጠኝ አንድ ወንበር አይመጥነኝም አለ

ባይቶና በምርጫው የተሰጠኝ አንድ ወንበር አይመጥነኝም አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የትግራይ ክልል ምርጫ ላይ ከተሳተፉት ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው ባይቶና አባይ ትግራይ የተሰጠን ወንበር አይገባንም ማለቱ ተሰማ።

“የምርጫው ፍትህዊነትና ዴሞክራሲያዊነት ተበላሽቷል” ያለው በተቃዋሚ ስም ህወሓት እንዳቋቋመው የሚነገርለት ባይቶና በውጤቱ የተሰጠን ወንበር ለእኛ አይገባም ብሏል።
በአዲሱ የክልሉ ምክር ቤት የመቀመጫ ድልድል ሕግ መሠረት ህወሓት ካገኛቸው 152 የምክር ቤት መቀመጫዎች በተጨማሪ 38 ወንበሮች ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ይከፋፈላሉ ቢልም፤ የምርጫ ኮሚሽኑ ባወጣው ውጤት መሠረት ህወሓት 189 ወንበሮች ሲያገኝ 1 ወንበር ደግሞ ባይቶና ማግኘቱ ተሰምቷል።
“ውሳኔውን ባንቀበለውም ሕግን እናከብራለን። በሕጉ መሠረት ደግሞ ይህ ወንበር ለእኛ ይገባናል ብለን አናምንም” ሲል ዛሬ መግለጫ የሰጠው ባይቶና፤
የትግራይ የምርጫ አዋጅ ከመጀመሪያውም ህወሓትን ለማገልገል የወጣ ነው ብለን እናምናለን በማለት ተሻሻለ የተባለውን የክልሉን ምርጫ ህግ ተችቷል።
“ይሁን እንጂ በቀመሩ መሠረት እኛ የደርስንበት የተሰጠን የሕዝብ ድምፅ ወንበር ለማግኘት የሚበቃ እንዳልሆነ ነው፤
ግን ለእኛ እንደሚገባ የሚያረጋግጥ የሕግ አገባብ ወይም ስሌት ካለ የተሰጠንን ወንበር በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ ነን ” ያለው ድርጅቱ፤ የትግራይ ሕዝብ ምርጫውን ለማሳካት ላደረገው አስተዋፅዖ ክብር አለኝ ብሏል።

LEAVE A REPLY