የኢትዮጵያ መንግስት እና አዳዲስ የብር ኖቶች || ፍሬህይወት ሳሙኤል (የህግ ባለሙያ)

የኢትዮጵያ መንግስት እና አዳዲስ የብር ኖቶች || ፍሬህይወት ሳሙኤል (የህግ ባለሙያ)

የኢትዮጵያ መንግስት የብር ኖቶቹን መቀየሩ ጥሩ መሆኑን ከብዙ አቅጣጫ እየሰማን ነው፨ በዚህ አጋጣሚ በአንድ ወቅት ከማውቀው ጉዳይ ተነስቼ ስጋቴን ለመግለፅ ፈልጋለሁ።

ጉደዩ እንደሚከተለው ነው፤  ጊዜው 1998 ዓ.ም ሆኖ አዲስ አበባ ውስጥ ለሰባት ወራት ሙሉ ጊዜዬን የምርመራ ስራዬን በምሰራበት ወቅት ነበር። “አንድ የምእራብ አፍሪካ ትንሽ አገር (ስሙን ለጊዜው እዚህ ከመጥቀስ ልቆጠብ) ዲፕሎማቶች ዲፕሎማቲክ ሻንጣ ውስጥ ብዙ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ጭነው በአዲስ አበባ ውስጥ ካሉት ኢትዮጵያውያን ህገወጥ የዶላር አዘዋዋሪ መረብ ጋር አየተመሳጠሩ የቦሌን ፊተሻ እያሳለፉ አዲስ አበባ ውስጥ ለተለያየ ህገ ወጥ ስራ እያዋሉ መሆኑን ሰማሁ፤ ጉዳዩን ጠለቅ ብዬ ጠያይቄ ማወቅ እንደቻልኩት ከአንድ ሀገር በላይ ይሳተፍበታል።

አዲስ አበባ በምርጫ 1997 ሁከት ምርምራ ወቅት ይህን ጉዳይ ከወሬ ያለፈ መሆኑን ለማወቅ የቻልኩበት ልዩ አጋጣሚ ተፈጥሮልኝ ስለነበር እና በዚህ ጉዳይ እየተሳተፉ የነበሩ የውጭ ዜጎችን እሜልና የተለዋወጡዋቸውን መልዕክቶች ከማግኘት አልፎ አስር ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በተግባር በቦሌ ሲያልፍ የነበረበትን ሂደት በዝርዝር “ አውቄም አረጋግጬም” ነበር።

በወቅቱ የዚህ ነገር አደገኛነት አሳስቦኝ ለፌዴራል የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ወርቅነህ ገበየሁ ደውዬላቸው “በምእራብ አፍሪካ ዲፒሎማቶች የሚታገዝ የህገወጥ ዶላር ዝውውር አዲስ አበባ ውስጥ አደገኛ ደረጃ መድረሱን ገልጬ አንድ ነገር ቢደረግ ይሻላል ስላቸው፤ ኮሚሽነር ወርቅነህም “ መንግስት ጉዳዩን እንደሚያውቅ፤ ነገር ግን የምዕራብ አፍሪካ ዲፒሎማቶችን ስንከታተላቸውና ጉዳዩን ስናነሳባቸው ‘እናንተ ድሮውንም እኛ ላይ ንቀት አለባችሁ፤ ውጡ ማለት ፈልጋችሁ ከሆነ እቅጩን ንገሩን እንሄድላችሗለን እያሉ የዲፕሎማሲ ጫጫታ እየፈጠሩብን አስቸግረውን ነው” ብሎ ስልኩን ጨረሰ።

በዚያው ሰሞን አንድ ቤት እያፈላለግኩ ሳለሁ ስሙን ያማለስተውሰው ሰው ከኢምፔሪያል ሆቴል ጀርባ ገባ ቢሎ ወደ አንድ ትንሽ መደብር በእጁ እየጠቆመ “ XXXX ባንክ የውጭ ገንዘብ የሚመነዝርበት ቦታ ስትደርስ ወደ ግራ ታጠፍ” አለኝ፨ ቦታው ስደርስ ትንሽ ቡቲክ አየሁ (ተራ ሱቅ ናት) ግን ከአንድ የግል ባንክ ጋር ተቀናጅቶ ዶላር የሚሰበሰብበት ቡቲክ፨ ከዚያ በሗለ ነገሩ ተራ ጉዳይ ሳይሆን የተደራጀ እና በመንግስት መዋቅር የሚደገፍ እንዲሁም በዙሪያው ማንም በወቅቱ የማይዳፈረው የወንጀል መረብ መኖሩን ፍንጭ ስላገኘሁ ይህን የኢኮኖሚ ወንጀል (ህገወጥ የዶላር ዝውውር) በማስቆም ረገድ አገራችንን ይረዱ እንደሆነ በማሰብ በወቅቱ የአሜሪካን ከፍተኛ ዲፕሎማት (ተጠባባቂ አምባሳደር) ለነበሩት ወ/ሮ ቪኪ ሀድልተን በአሜሪካ ኢምባሲ በአካል ተገናኝተን አንስቼ ነበር።
አሁን ይህን ጉዳይ ማንሳት ያስፈለገበት ሁለት ምክንያቶች አሉኝ።
1ኛ፡ ከላይ እንደገለፅኩት ዶላርም ሆነ ሌላ የውጭ ገንዘብ በማስገባትም ሆነ በማስወጣት በሚታሙ የውጭ ሃገር ኢምባሲዎች አከባቢ አሁንም ችግሩ የቆመ ስላልመሰለኝ ለማሰሰብ ነው።  የአየር መንገድ አንዳንድ ሰራተኞችም በዝህ ሂደት ተሳታፊ ስለነበሩ መንግስት የሚያውቀውም ቢሆን መናገሩ ለሃገር ይጠቅም ይሆናል ብዬ ነው።
2ኛ፡ የግል ባንኮች ብሩ መቀየሩ በተነገረበት እለት ያላቸው ባላንስ ሽት መታወቅ ያለበት ይመስለኛልገ የሀሰት ኖት የማሳተም ስራ ተባባሪ ናቸው የሚባሉ የግል ባንኮችን ስም እየሰማን ስለሆነ ይህ እውነት መሆን አለመሆኑ ቢረጋገጥ (ኖቶች ስለመታተማቸው በግልፅ የሚታወቅ ስለሆነ አታሚውና ተባበሪዎቻቸው ቢታወቁ እና በህግ ቢጠየቁ) ፤ መንግስት አኛ በግለሰብ ደረጃ የምናውቀውን የሀሰት ኖት ህትመት ጉዳይ ‘አላውቅም’ ካለ እኔ እንደ ግለሰብ ለማገዝ ዝግጁ ነኝ።

(ይህ ጉዳይ ግለሰባዊ ቢሎም መንግስታዊ (በመዋቅር የሚታገዝ) መንጀል ስለሆነ አንድን የግል ባንክ ስም በፌስ ቡክ በመለጠፍ የሚፈታ ችግር ስላልመሰለኝ የባንኩን ስም ማንሳት አላስፈላገኝም፤ በየሰፈሩ የተሰማሩ ነጭ ለባሻ የመንግሰት ደህንነቶች ይህን አላወቁም/አያውቁም/ እና እኔ ልንገራቸው ብዬ እራሴን ማሞኘትም አልፈልግም፨ ግን ስለ ሃገሬ ያሚሰማኝን ጥልቅ ስጋት በሀላፊነት ስሜት ለመግልፅ ያህል ነው። )

በሌላ በኩል ቢቻል ከተወሰነ የገንዘብ መጠን በላይ (ለምሳሌ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ) ብር ይዞ ለመቀየር የሚመጣ ሰው የገንዘቡን ምንጭና ግብር የተከፈለበት ገቢ መሆኑን ፎርም (ቅፅ) ከቃለ መሃላ ጋር እንዲሞላ ተደርጎ ሗላ ፋታ ሲገኝ ቢጣራና ህገወጥ ገንዘብ ለመቀየር ባመጡት ላይ ህጋዊ ውሳኔ ቢሰጥ።

ካልሆነ አሁን አገርቱ ውስጥ ተደራጅቶ ያለው የኢኮኖሚ አሻጥር በብር ለውጥ ምክንያት ቅርፁን እንጂ ይዘቱን ላይቀይር ይችላል የምል የግል ስጋት አለኝ፨

LEAVE A REPLY