ዶክተር ዐቢይ የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትንና ጊቤ 3 ኃይል ማመንጫን ጎበኙ

ዶክተር ዐቢይ የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትንና ጊቤ 3 ኃይል ማመንጫን ጎበኙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የዳውሮ ተፈጥሯዊ ሀብቶችንና በኮይሻ ወረዳ እየተገነባ ያለውን የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን መጎብኘታቸው  ተነገረ።

በገበታ ለሀገር ፕሮጀክት እንደሚለሙ ከተገለጹት አካባቢዎች መካከል አንዱ የሆነው የኮይሻ ኃይል ማመንጫ፤ በጠቅላይ ሚኒስትሩና በልዑካቸው የተጎበኘ ሲሆን፣ ከኮይሻ እስከ ንጉስ ሀላላ ኬላ ያሉ የተፈጥሮ መስህቦች የጉብኝቱ አካል ነበሩ።
የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አጠቃላይ አፈፃፀም በአሁኑ ወቅት 36 በመቶ ላይ የደረሰ ሲሆን፣ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ 2 ሺኀ 160 ሜጋዋት የማመንጨት አቅም ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተያያዥነት የጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ ግድብንም መጎብኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።
ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ የሀገሪቱን የኃይል አቅርቦት እስከ 60 በመቶ እየሸፈነ የሚገኝ ትልቁ ኃይል ማመንጫ መሆኑ ይታወቃል።

LEAVE A REPLY