ኢዜማ ለህዳሴው ግድብ የግማሽ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

ኢዜማ ለህዳሴው ግድብ የግማሽ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና|| የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ግማሽ ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

በቅርቡ በከተማዋ የተካሄደውን የመሬት ምዝበራና ሕገ ወጥ የኮንዶሚኒየም እደላን በማስረጃ ያጋለጠው የኢዜማ ዋና መሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፤ እንደዚህ አይነት ድጋፍ በማድረግ ለሀገር ትልቅ ፋይዳ ያላቸው ትልልቅ ፕሮጀክቶችን መደገፍ ለሃገር ሰፊ ትርጉም አለው ብለዋል።
ምንም እንኳን በፓለቲካ ባህላችን የአቋም ልዩነት ቢኖርም፣ የጋራ የሚያደርጉን ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ በአንድነት መቆም ይኖርብናል ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፤ ፓርቲያቸው በቀጣይም ሃገራዊ ራዕይ ያላቸው እንቅስቃሴዎች ላይ አቅም በፈቀደ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።
ኢዜማ የግማሽ ሚሊዮን ብር ድጋፉን ያደረገው በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሃገር ላይ የሚገኙ አባላቱ ባበረከቱት ስጦታ መሆኑንም ገልጿል።

LEAVE A REPLY