የእነ ታከለ ኡማ ሹመት በፓርላማው ፀደቀ

የእነ ታከለ ኡማ ሹመት በፓርላማው ፀደቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና|| የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ያቀረቡትን የሚኒስትሮች ሹመት አፀደቀ።

ከሳምንታት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትሩ በተካሄደው ሹም ሹር አዳዲስ ሹመት የተሰጣቸው ሚኒስትሮች እንደከዚህ ቀደሙ በፓርላማው ፊት ቃለመሀላ ሳይፈፅሙ ነበር ።
ዛሬ ዘግይተውም ቢሆን ሹመታቸው የፀደቀው ሚኒስትሮች፦
1. ዶ/ር ቀነዓ ያዴታ የኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር
2. ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
3. ዶ/ር ሳሙኤል ሁርቃቶ የኢፌዴሪ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር፣
4. ኢንጅነር ታከለ ኡማ የኢፌደሪ ማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ሚኒስትር ናቸው።
 ምክር ቤቱ የቀረበውን ሹመት በአምስት ድምፀ ተዐቅቦ፣ በአብላጫ ድምጽ የሚኒስትሮችን ሹመት አጽድቋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ምክር ቤቱ የ40 የከፍተኛ ፍርድ ቤት እጩ ዳኞችን ሹመት በ5 ድምፀ ተዐቅቦ ፣ በአብላጫ ድምፅ ፣ እንዲሁም የ50 የመጀመሪያ ፍርድ ቤት እጩ ዳኞችን ሹማት ደግሞ በ3 ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ያፀደቀ ሲሆን፤ እጩ ዳኞቹም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ አማካኝነት በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መለላ መፈጸማቸው ታውቋል።

LEAVE A REPLY