ልደቱ አያሌው በ100 ሺኅ ብር ዋስትና እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ ወሰነ

ልደቱ አያሌው በ100 ሺኅ ብር ዋስትና እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ ወሰነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና|| ከሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በቢሾፍቱ ከተማ አመፅና ኹከት እንዲነሳ ድጋፍ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩት አቶ ልደቱ አያሌው በ100 ሺኀ ብር ዋስ እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ ወሰነ።

ኹከት በመፍጠር የተጠረጠሩት ሌደቱ አያሌውን ክስ ከሳምንት በፊት የቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ ሕገ ወጥ መሣሪያ ይዞ በመገኘት ክስ እንደመሠረተባቸው ይታወቃል።
በዚህ የተነሳ በእስር ላይ የነበሩት  ልደቱ አያሌው ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር። በችሎቱ አቶ ልደቱ ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ የተቀበለው ፍርድ ቤቱ፤ ተጠርጣሪው በአንድ መቶ ሺኅ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ መወሰኑን ጠበቃቸው አቶ አዲሱ ጌታነህ ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY