ኢትዮጵያ ነገ ዜና|| የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በ7 ግለሰቦች ላይ ዐቃቤ ህግ ያቀረበውን ክስ እንዲያሻሽል ትእዛዝ ሰጠ።
ችሎቱ ዛሬ ዐቃቤ ህግ በእነ እስክንድር ዙሪያ የቀረበውን ክስ እንዲያሻሽል ያዘዘው፦ በሰኔ 23 እና ሰኔ 24 2012 ዓ.ም በሰው ላይም በንብረት ላይም ደረሰ የተባለው ጉዳት ተለይቶ እንዲቀርብ፣ እንዲሁም የደረሰው ጉዳት ቦታው የት እንደሆነ? በየት ክፍለ ከተማ እና ወረዳ፣ በስንት ሰዓት? የሚለው በደንብ እንዲገለፅ የሚል ነው።
በተጨማሪም ቦታው ከታወቀም በኋላ የተከሳሾቹ የወንጀል ተሳትፎ በዝርዝር ተለይቶ እንዲቀርብ ፍርድ
ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቷል።
በዚህ የተላለፈው ትእዛዝ መሠረት ዐቃቤ ሕግ በሳምንት ውስጥ ክሱን አሻሽሎ ለመስከረም 19 2013 ዓ.ም ጠዋት ክሱን አሻሽሎ እንዲያቀርብ በችሎት ፍርድ ቤቱ አዟል።
በችሎቱ የተገኙት የእነ አቶ እስክንድር 4 ጠበቆች ማረሚያ ቤት ከቤተሰብ ጋር እያገናኛቸው እንዳልሆነ፣ ምግብ እና ልብስም እየገባላቸው አለመሆኑን ገልጸዋል።
ጠበቆቹ ሌሎች አቤቱታዎችን ለማቅረብ ቢጠይቁም፤ ፍርድ ቤቱ ጥያቄያችሁ በችሎት ተመዝግቦ የሚሄድ አይደለም፤ ክርክር አንዳይነሳበት በማለት፣ ጊዜ የማይሰጡ የህክምና እና በቤተሰብ መጎብኘት ያለባቸውን ማረሚያ ቤቱ እንዲፈፅም ትእዛዝ መስጠቱ ታውቋል።