ዶ/ር ቴድሮስ እና አርቲስት አቤል ተስፋዬ የታይም መጽሔት 100 ተፅዕኖ አሳዳሪዎች ውስጥ...

ዶ/ር ቴድሮስ እና አርቲስት አቤል ተስፋዬ የታይም መጽሔት 100 ተፅዕኖ አሳዳሪዎች ውስጥ ተካተቱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና|| የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን መቆጣጠር አለመቻሉን ተከትሎ በአሜሪካ ግፊት ከሓላፊነታቸው እንደሚነሱ ሲናገር የነበረው የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም እና ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዓለም ዐቀፍ ድምፃዊ አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊክንድ) በ2020 የታይም መጽሔት መቶ ተፅዕኖ አሳዳሪዎች ውስጥ መካተታቸው ተሰማ።

ዶክተር ቴዎድሮስ በመሪዎች ዘርፍ፣ እንዲሁም ድምፃዊ አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊክንድ) በአርቲስቶች ዘርፍ ነው ከመቶ ተፅዕኖ አሳዳሪዎች መካከል ለመካተት የበቁት።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በየትኛው የዓለም ክፍል የሚገኝ ማንኛውም ሰው ጥራት ያለው የጤና እንክብካቤ ማግኘት አለበት የሚል ጠንካራ አቋም እንዳላቸው ታይም መጽሔት አብራርቷል።
ዶክተር ቴዎድሮስ በዲሞክራቲክ ኮንጎ በተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ምላሽ ላይ በግል ኃላፊነታቸውን መወጣታቸው የተጠቀመ ሲሆን፤ ይህም በዓለም ዐቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስን መከላከል ላይ ተስፋና እና ጠንካራ ዓለማ እንዲኖራቸው አስችሏልም ብሏል።
ሁለተኛው ተፅዕኖ አሳዳሪ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ፣ የካናዳ ዜግነት ያለው አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊክንድ) በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ተወዳጅነትን እያተረፈ የመጣ ድምፃዊ፣ ገጣሚ እና የሙዚቃ ፕሮዲውሰር መሆኑን ከታይም መጽሔት ዝርዝር መረዳት ተችሏል።

LEAVE A REPLY