ናፍቆትሽ ፀናብኝ
ብየ ስልክልሽ
‘አይዞህ ‘ አይባልም
መከሰት ነው እንጂ በገሀድ ወይ በህልም !
ካጨሽ አሰናብቺ
ትዳር ካለሽ ፍቺ
ለኔ ለምመኝሽ ሁሉን ነገር ስጪ
የህሊና ቀጪ
የልቦና ስሜት
ይሉንታና ሀሜት
ያገር ሰው ሽሙጥም
ከምኞቴ አይበልጥም ::
ተሊቀመላኩ
ክንፍ ተበድረሽ
ነፋስ ቀድመሽ በረሽ
ባለሁበት አገር
እንደ ሸዋዚንገር
ብረት ለበስ ጡንቻ
ባንድ ርግጫ ብቻ
የቤቴን በር ሰብረሽ
ዐይነ ርግብሽ ወድያ
ቀሚስሽ ወደ ላይ
ወደኔ በጥድፍያ
ወዳልጋው በዝላይ
በጀርባየ ሁኘ
ከእግሮቼ መካከል የጠላ ምልክት
አንቺ ጆሮ ሆነሽ
እኔ ሎቲ ሆኘ-ተጣጥሞ ስክት !
እንዲህ እያሰበ ገላየ ሲቸገር
መጣሁ ትያለሽ ስል
“አይዞህ “ ብሎ ነገር፤
የማለዳ ራእይ፤ ምኞቴን በማመን
በገሀድም ይሁን፤ ወይም በሰመመን
አሳትፊኝ አልሁ እንጂ
ከገላሽ በረከት፤ ከሙቀት ከለዛው
የቃል ምፅዋትማ ሞልቷል በየታዛው!