ኦፌኮ የአማራና የኦሮሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች ፈጸሙት የተባለው ስምምነት ውስጥ የለሁበትም አለ

ኦፌኮ የአማራና የኦሮሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች ፈጸሙት የተባለው ስምምነት ውስጥ የለሁበትም አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ዐሥር የኦሮሞና የአማራ የፖለቲካ ድርጅቶች ባለፈው ዓመት የጀመሩትን ድርድር ተከትሎ በልዮነቶቻቸው ላይ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል የተባለው መግለጫ ውስጥ ኦፌኮ አለመኖሩን ገለጸ።

ጃዋር መሐመድን ባለፈው ዓመት በአባልነት የተቀበለው፣ በበቀለ ገርባና መራራ ጉዲና የሚዘወረው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) የአማራና የኦሮሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች  ለ10 ወራት ያህል በተለያዩ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ሲወያዩ ቆይተው በ10 ነጥቦች ላይ ተስማምተዋል ተብሎ የተገለጸው ዝርዝር ውስጥ ስለመኖሩ በሁሉም ሚዲያዎች ሲገለጽ መቆየቱ አይዘነጋም።
ዛሬ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ባወጣው መግለጫ  ላይ፤ ሲቀርቡ የነበሩትን ዘገባዎች በማስተባበል፣ ስብሰባዎቹ ኅብረተሰባችንን ጥቅም የሚያስጠብቅና ለፊርማ የሚበቃ ደረጃ ላይ ስላልደረሰ ፊርማዬን አላኖርኩም ሲል ገልጿል።
የፓርቲው ሊቀመንበር ፕ/ር መረራ ጉዲና በሸራተን አዲስ በተካሄደውና ተፈረመ በተባለው ስምምነት ላይ ፤ ፓርቲያቸው እንዳልተወከለም ለኢትዮጵያ ቼክ ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY