ኢትዮጵያን ጨምሮ ወደ አሜሪካ የሚሄዱ አፍሪካውያን ተማሪዎች ቪዛ በ2 ዓመት ሊገደብ ነው

ኢትዮጵያን ጨምሮ ወደ አሜሪካ የሚሄዱ አፍሪካውያን ተማሪዎች ቪዛ በ2 ዓመት ሊገደብ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አሜሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከበርካታ አፍሪካ አገራት የሚመጡ ተማሪዎችን አስመልክቶ አዲስ ረቂቅ መመሪያ አቀረበች።

በዚህም ረቂቅ መሰረት የተማሪዎቹ ቪዛ በሁለት አመት እንዲገደብ ሲሆን፤ በአዲሱ ረቂቅ መሠረትም ተማሪዎቹ የትምህርት ጊዜያቸውን ሳያጠናቅቁ የቪዛ ጊዜያቸው ያልቃል።
በአሜሪካው ሆምላንድ ሴኩሪቲ ቢሮ እንደወጣ የተነገረለት መመሪያ፤ ከዚህ ቀደም ተማሪዎች ትምህርታቸውን እስኪያጠናቅቁ ድረስ ይሰጥ የነበረውን የቪዛ ህግ ሙሉ ለሙሉ የቀየረ ነው።
የአራት አመት ቪዛ የሚሰጣቸው አገራትን ዝርዝር ያካተተው ረቂቁ፤ በሁለት አመት የሚገደብበት አንደኛው ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ ማጭበርበርና ብሄራዊ ደህንነት ስጋት መፍጠሩን ተከትሎ እንደሆነ ያሳያል።
የብሄራዊ ደህንነት ስጋት ተብለው ከተጠቀሱት ሃገራት መካከል ሽብርን በመደገፍ የምትጠረጥራቸው እንደ ሱዳን ያሉ ሃገራት የሚመጡ ተማሪዎች ላይ ተፅእኖ ይደርሳል እየተባለ ነው።
ቪዛው ከሚፈቅድላቸው በላይ የቆዩ ተማሪዎችን በአማካኝ አስልቶም 10 ከመቶ በላይ የቆዩ ሃገራት ዜጎችን በሁለት አመታት እንዲገደብ የሚመክር ሲሆን፤ የኢትዮጵያና የናይጄሪያ ተማሪዎች ከ13 በመቶ በላይ እንደቆዩም መረጃው የጎሮጎሳውያኑን 2019 መረጃን ዋቢ በማድረግ ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY