ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የዓለም የጤና ድርጅት ሁነኛ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት እስኪገኝ ድረስ በዓለም ዙሪያ 2 ሚሊዮን ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ ሲል ግምቱን አስቀመጠ።
በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ብዛት ወደ 1 ሚሊዮን እንደተጠጋም ሬውተርስ ይፋ አድርጓል።
የድርጅቱ የአጣዳፊ ጉዳዮች ሓላፊ የሆኑት ማይክ ሪያን የተረጋገጠ ክትባት እስኪገኝ ድረስ አነሰ ቢባል 2 ሚሊዮን ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሊሞቱ እንደሚችሉ ይናገራሉ።
በዚህ ወቅት በርካታ ክትባቶች በተለያየ የሙከራ ደረጃ ላይ ሲሆኑ፤ ድርጅቱ ሁነኛ ክትባት ሲገኝ ለድሃ ሃገሮች እንዲዳረስ ኮቫክስ የተሰኘ የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር መዘርጋቱን ለማወቅ ተችሏል።
ቻይናም ይህንን ድጋፍ ማሰባሰቢያ በዋናነት እንድትደግፍ ምክክር እየተደረገ ነው ያሉት ማዬክ ሪያን፤ እስከዚያው መሰረታዊ የመከላከያ መላዎች ቸል መባል እንደሌለባቸው ገልጸዋል።