ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ኢንስትራክተር አብርሃም መብራህቱን ያሰናበተው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ ውበቱ አባተን ቀጠረ።
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው በሁለት ዓመት ኮንትራት መሾማቸውን ፌዴሬሽኑ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋ ተደርጓል።
አዲሱ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ውበቱ በውላቸው ውስጥ ለአፍሪካ ዋንጫ የማለፍ እና ለዓለም ዋንጫ መለያ ጨዋታ (ፕሌይኦፍ) የመድረስ ግዴታ የተጣለባቸው ሲሆን፣
በቆይታቸውም ያልተጣራ 212 ሺኅ ብር (125 ሺ የተጣራ) ወርሀዊ ክፍያ ያገኛሉ ተብሏል።
ከዚህ በተጨማሪ አሠልጣኝ ውበቱ 1 የግብ ጠባቂ እና 2 ረዳት አሠልጣኞችን በራሳቸው መርጠው ለፌዴሬሽኑ እንዲያስታውቁ መብት ተሰጥቷቸዋል።
አዝናኝ እግር ኳስ የሚጫወተው ኢትዮጵያ ቡና 2003 ዓ.ም በፕሪምየር ሊጉ የመጀመሪያው የሆነውን ዋንጫ እንዲያገኝ ያስቻለው አሰልጣኝ ውበቱ አባተ አምና ፋሲል ከነማ የፕሪሜየር ሊጉ የዋንጫ ተፎካካሪ ሆኖ እሰከመጨረሻው ጨዋታ በአስደናቂ ብቃት እንዲዘልቅና ሁለተኛ ሆኖ እንዲጨርስ እንዲያጠናቅቅ ማድረጉ አይዘነጋም።