ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሦስት የውጭ ቋንቋዎችን በቀጣዮ ዓመት በሁሉም ት/ቤቶች መስጠት እንደሚጀምር አስታወቀ።
ዛሬ ይፋ በሆነው የክልሉ ትምህርት ቢሮ መግለጫ ላይ፤ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቤቶች ቻይናኝን ጨምሮ ፈረንሳይኛና ጀርመንኛ ቋንቋዎችን ተማሪዎቻቸውን በመደበኛነት ያስተምራሉ።
በቀጣዮ ዓመት (2014 ዓ.ም) ተግባራዊ የሚደረገው አዲሱ ፍኖተ ካርታ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው አንዲማሩ በሚያዘው መልኩ ክልሉ ከሚያስተምረው ኦሮምኛና አማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ የሶማሊኛ ቋንቋን አካቶ እንደሚያስተምር ነው የተገለጸው።
ኦሮሚያ ክልል ከሶማሌ ክልል ጋር በድንበር የሚዋሰን ከመሆኑ ባሻገር በንግድና በሌሎች ማኅበራዊ ትስስሮች ዘመናት የዘለቀ ግንኙነት ያለው በመሆኑ ሶማሊኛ ቋንቋን በመደበኛ ትምህርትነት በኦሮሚያ ክልል መስጠት ፋይዳው የጎላ ነው ያለው የክልሉ ትምህርት ቢሮ፤ ዓለም በተለያየ መንገድ አንድ እየሆነ ከመምጣቱ አኳያ ሦስቱን የውጭ ቋንቋዎች ማስተማር በእጅጉ ጠቃሚ ሆኖ ተገኝቷል ብሏል።