አሜሪካ 2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ በስጦታ አበረከተች

አሜሪካ 2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ በስጦታ አበረከተች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አሜሪካ 2 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር የሚያወጡ የልምምድና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቀሶችን ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ማድረጓን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ይፋ አደረገ።

ድጋፉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው አልሸባብ የሽብር ቡድን እና ሌሎች የሽብር ድርጅቶችን ሊፈጥሩት የሚችሉትን አደጋዎች ለመመከት ያግዛታል ተብሏል።
የአሜሪካ መከለከያ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር ጋር በትብብር እየሠራሁ ነው ያለው ኤምባሲው፤ በተያዘው ዓመት የተደረገው ድጋፍም የዚሁ አካል ነው ሲል ገልጿል።
የአሜሪካ መንግሥት ለኢትዮጵያ ድጋፍ ያደረገው፤ አምቡላንስ ፣ ላንድ ክሮዘር ፣የእቃና የነዳጅ መጫኛ ተሸከርካሪዎችን እንዲሁም የምሽት አጉሊ መነፅርን ያካተተ እንደሆነ ታውቋል።

LEAVE A REPLY