ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ነገ መስከረም 20 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 1 ሰዐት ከ30 እስከ 6 ሰዐት 30 ድረስ በመስቀል አደባባይ የሰልፍ ትርዒት እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
“ከራስ በላይ ለሕዝብና ለሀገር” በሚል መልዕክት የፖሊስ አገልግሎት አሰጣጥ ዝግጁነት የደረሰበትን ደረጃ የሚያሳይ ልዩ ልዩ ፕሮግራሞችን እያደረገ እንደሚገኝና ነገ የመንግሥት ከፍተኛ ሓላፊዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የሰልፍ ትርዒቱ እንደሚቀርብ ታውቋል።
ይህን ተከትሎ፦ ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ፣ ከደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ፤ ከመገናኛ፣በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ፣ ከቦሌ መድኃኒዓለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ፣ ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻ ወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት የይለፍ ፈቃድ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ እንደሚሆኑ ከወዲሁ ተነግሯል።
በተጨማሪም ከቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሃገር አስተዳደር መብራት ወይም ኢሚግሬሽን መሥሪያ ቤት አካባቢ፣ ከተክለሃይማኖት በሜትሮሎጂ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መሥሪያ ቤት አካባቢ፣ ከተክለሃይማኖት፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ ኢሚግሬሽን ጥቁር አንበሳ የኋላ በር፣ ከጌጃ ሰፈር፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ፣ ከሳሪስ በጎተራ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ፣ ከጦር ኃይሎች፣ልደታ፣ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ፤ ከጦር ኃይሎች፣ ልደታ፣ፖሊስ ሆስፒታል፣ ሜክሲኮ ፣ ለገሀር መብራት የሚወስደው ለገሃር መብራት ዝግ መሆኑ ታውቋል፡፡
ለዚህም አሽከርካሪዎች የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልእክት ተላልፏል።