ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ የፖሊዮ በሽታ ምልክት ዳግም በመታየቱ እድሜያቸው ከ 5 አመት በታች ለሆኑ 7 ሚሊዮን ሕጻናት ክትባት ሊሰጥ መሆኑ ተነገረ።
ኢትዮጵያ በ2011 ከፖሊዮ በሽታ ነፃ ሆናለች ቢባልም በጎረቤት ሀገራት በሽታው ተከስቶ በሱማሌ ክልል በበሽታው የተያዙ ህፃናት መገኘታቸውን የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት አስታውቋል።
በኦሮሚያ ክልልም ከታህሳስ 2011 ዓ.ም ጀምሮ ቤት ለቤት በተሠራ ዳሰሳ 3 ሰው ላይ የፖሊዮ አምጪ ተህዋስ መገኘቱ እየተነገረ ነው። ስለበሽታው ቀደም ሲል ስጋት አለባቸው በተባሉ በእነዚሁ ክልሎች ሙሉ በሙሉ ባይዳረስም ክትባቱ መሰጠቱም ታውቋል።
አሁን ላይ ክትባቱን ሙሉ ለሙሉ ለማዳረስና በዘመቻ ለማካሄድ ስጋት አለባቸው በተባሉ ሱማሌ፣ ደቡብ ፣ ኦሮሚያና ሀረሪ ክልሎችና አዲስአበባ ፣ እንዲሁም ድሬደዋ ለሚገኙ 7ሚሊየን ሕፃናት ይሰጣል ተብሏል።
የክትባት ዘመቻው ከመስከረም 27 እስከ 30 ቤት ለቤት ለዐራት ቀናት እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለዉ አባይነህ ዛሬ ተናግረዋል።
በተያያዘ ዜና በደቡብ ክልል ባለፈው ዓመት የተከሰተውን የቢጫ ወባ ወረርሽኝ ተከትሎ 86 ሰዎች ሲያዙ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ ክትባት ተሰጥቶ የነበረ ቢሆንም፤
ነገር ግን አሁንም ቢሆን በክልሉ የቢጫ ወባ ስጋት በመኖሩ በክልሉ በሚገኙ 11 ወረዳዎች እና 1 በኦሮሚያ አጎራባች ወረዳ ለሚገኙ 704 ሺኅ ሰዎች ክትባት ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ተሰምቷል።
የቢጫ ወባ ክትባቱ በመጪው ጥቅምት 13 እንደሚሰጥ ሰምተናል።