የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከቀለም ትምህርት በተጨማሪ የሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ሊሆኑ ነው

የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከቀለም ትምህርት በተጨማሪ የሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ሊሆኑ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ከቀለም ትምህርት በተጓዳኝ የሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ሊሆኑ መታቀዱ ተሰማ።

ትምህርት ሚኒስቴር ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብትና ቴክኖሎጂ፣ እንዲሁም የግብርና፣ አርብቶ አደርና አካባቢ ጥበቃ  የቋሚ ኮሚቴዎች ጋር በትምህርት ዘርፉ እየተካሄዱ ባሉ ዋና ዋና ሪፎርሞችና የቀጣይ 10 ዓመት እቅድ ላይ ውይይት እያካሄደ ነው።
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ በትምህርት ዘርፉ ከሚካሄዱ ሪፎርሞች ውስጥ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከቀለም ትምህርት በተጨማሪ የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን የሙያ ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችሉ ተቋማት እንዲሆኑ የስርዓተ ትምህርት ሪፎርም እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በትምህርት ዘርፉ እየተደረጉ ባሉት ሪፎርሞች ተግባራዊነት ላይ ሓላፊነታቸውን እንዲወጡም የትምህርት ሚኒስትሩ መልእክት አስተላልፈዋል።
የትምህርት ዘርፉ ሪፎርም ሥራዎችን የሚያሳዩ ሰነዶች ቀርበው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ውይይት እየተደረገባቸው መሆኑን ሰምተናል።

LEAVE A REPLY