አዲስ አበባ አሁንም በመከላከያ፣ በሪፐብሊካን ዘብና በፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ ቁጥጥር ሥር ነች

አዲስ አበባ አሁንም በመከላከያ፣ በሪፐብሊካን ዘብና በፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ ቁጥጥር ሥር ነች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ነውጠኛና ጽንፈኛ ብሔርተኛ ቡድኖች ከመስከረም 30 2013 ዓ.ም በኋላ መንግሥት የለም የሚሉ ኹከት ናፋቂ ፖለቲከኞችና ድርጅቶች የሚነዙትን ከፍተኛ ፕሮፐጋንዳን ተከትሎ አዲስ አበባ ከወትሮው በተለየ ልዮ ጥበቃ እየተደረገላት ይገኛል።

በተለይም በጃዋር መሐመድ የሚመራው ጽንፈኛ ቡድን ባለፈው ዓመት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ስድስተኛው ሃገራዊ ምርጫ እንዲራዘም በሁለቱም ምክር ቤቶች  ከተወሰነ በኋላ፤ በሀሳብና በግብር ከሚመስሉት ጋር ከመስከረም መጨረሻ በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት በሥልጣን ላይ መቀጠል አይችልም በሚል ይፋዋ ጦርነት ሲያውጅ መሰንበቱ አይዘነጋም።
ከእነዚህ አመራሮች ፖለቲከኞችና አመራሮች መሀል የተወሰኑት ከሀጫሉ ግድያ ጋር በተያያዘ አጋጣሚውን ለሚፈልጉት መንግሥት የመናድ እቅድ ሊጠቀሙበት (ከእስክንድር ነጋ ወጪ) ሙከራ አድርገዋል በሚል በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውለው ክስ ቢመሰረትባቸውም፣ ግብረአበሮቻቸው የመንግሥት የለም ጥያቄን ከማስተጋባት ባሻገር፣ እስረኞች ይፈቱ የሚል ከፍተኛ ግርግር ሲፈጥሩ እየታየ ነው።
ይህንንና በቅርቡ ከኦነግ ሊቀመንበርነት የታገዱት ዳውድ ኢብሳ ከመስከረም 30 በኋላ መንግሥት ስለማይኖር ልናሰማራው ያዘጋጀነው ኃይል አለ የሚል አስተያየት መስጠታቸውን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ እና የተጠናከረ የፀጥታ ኃይል በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ሰፍሯል።
በተለይም የሪፐብሊካን ዘብና የመከላከያ ሠራዊት በከፍተኛ ሁኔታ ከትናንትና ጀምሮ አሁንም ድረስ በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች በመኪና ተደጋጋሚ ቅኝት እያደረጉ ይታያል። የፌደራል ፖሊስ አባላትም በቅርቡ በተገዛላቸው ባለነጭ ቀለም ታንክ መሰል የከተማ መኪና እጅግ አስፈሪ በሆነ መልኩ ከባድ መሣሪያዎችን ጭምር ታጥቀው በሁሉም የአዲስ አበባ አካባቢዎች እየተንቀሳቀሱ ነው።
ለወትሮው አዲስ አበባ ላይ በስፋት የሚታዮት የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት በየክፍለ ከተማዎቹ የሚገኙ መንደሮች ውስጥ በሲቪልና በደንብ ልብስ በመሆን ከፍተኛ ጥበቃ እንዲያደርጉ ትእዛዝ መተላለፉን የጠቆሙ ለተቋሙ ቅርበት ያላቸው ታማኝ የዜና ምንጮች፣ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት የአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብስን ለብሰው በቅኝት ሥራው ላይ እንዲሠማሩ መደረጉን ተናግረዋል።
ከሦስት ቀናት በፊት ጀምሮ ብዛት ያላቸው የብሔራዊ መረጃና ደሕንነት አባላት (ከኦሮሚያ ደሕንነት ቢሮ የተላኩትን ጨምሮ) ሁሉንም የከተማዋን ቦታዎች ያጥለቀለቁት መሆኑን ታማኝ የኢትዮጵያ ነገ ምንጮች ሹክ ብለውናል።

LEAVE A REPLY