ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ግዙፉ የባሕር ዳር ኢንዱርትሪ ፓርክ በይፋ ተመርቆ ሥራ መጀመሩ ተሰማ።
በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሓላፊዎች ተገኝተዋል።
ዛሬ የተመረቀው የባሕር ዳር የመጀመሪያው ምዕራፍ የኢንዱስትሪ ፖርክ 75 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን፣ ሁለተኛው ምዕራፍ የኢንዱስትሪ ግንባታ ደግሞ 125 ሄክታር መሬት ላይ እንደሚያርፍ ተገልጿል።
ፓርኩ በቅርቡም ከአራት ሺኅ በላይ ሠራተኞችን ለመቀበል ልየታ ማከናወኑ የታወቀ ሲሆን፤ በሙሉ አቅሙ በሁለት ፈረቃ መሥራት ሲጀምር 10 ሺኅ ለሚደርሱ ሰዎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ተነግሮለታል።