የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ የተለያዮ ውሳኔዎችን አሳለፈ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ የተለያዮ ውሳኔዎችን አሳለፈ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው በ6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አደራሽ ነበር ያከናወነው።
ፓርላማው ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መደበኛ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበን የድጋፍ ሞሽን አዳምጧል፡፡
ምክር ቤቱ በዛሬ ስብሰባው የንግድ ሕግ ረቂቅ አዋጅን፣  የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን፣ በኢትዮጵያ እና በራሽያ ፈዴሬሽን መንግሥት መካከል የኒውክሊየር ኃይልን ለሰላማዊ ዓላማ ለማዋል የተደረገውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን፣ የወንጀል ሕግ ሥነሥርዓት እና ማስረጃ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራቱም ታውቋል።
ከእነዚህ አራት አጀንዳዎችና ረቂቅ ሕጎች ባሻገር የምክር ቤቱን 5ኛ አመት የሥራ ዘመን 4ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ቃለ ጉባዔም መርምሮ ማፅደቁ ተሰምቷል።

LEAVE A REPLY