ለ150 ዓመታት በለንደን ሙዚየሞች የሚገኙ ከኢትዮጵያ የተዘረፉ ቅርሶችን ለማስመለስ ንግግር ተጀመረ

ለ150 ዓመታት በለንደን ሙዚየሞች የሚገኙ ከኢትዮጵያ የተዘረፉ ቅርሶችን ለማስመለስ ንግግር ተጀመረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በለንደን የሚገኘው ቪክቶሪያና አልበርት ሙዚየም ከ150 ዓመታት በፊት ከኢትዮጵያ ተዘርፈው የተወሰዱ ጥንታዊ ቅርሶችን ለመመለስ ድርድር መጀመሩ ተሰማ።
ሙዚየሙ ስለ ቅርሶቹ አመላለስ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር መነጋገር ጀምሬያሁ ማለቱን የገለጸው  ዘ ጋርዲያን፣ በቅርቡ ይህ እቅድ እውን ሊሆን እንደሚችልም ግምቱን አስቀምጧል።
የጥንታዊ ቅርሶች ማኖሪያና ቤተ-መዛግብት ለማቋቋም በዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ የነበረውን ህልም ለማሳካት የመቅደላ ተራራ በወቅቱ መመረጡን ተመርጦ የነበረ ቢሆንም፤ የእንግሊዝ ጦር ቦታውን ከተቆጣጠረ በኋላ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጦር ሲፈታ፤ ወዲያው ወደ ምዝበራ መግባቱን ለቁጥር የሚታክቱ ጥንታውያን ቅርሶች ተይዘው ከሀገር ሊወጡ እንደቻሉ ከታሪክ ድርሳናት መረዳት ይቻላል።
እነዚህ በተለያዩ የእንግሊዝ ታላላቅ ሙዚየሞች የሚገኙትን የኢትዮጵያ ቅርሶች ለማስመለስ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ቀርበው ነበር።
በደቡብ ምዕራብ ለንደን የሚገኘው የቪክቶሪያና አልበርት ሙዚየም ከሰሞኑ ባካሄደው የስነ ጽሑፍ ፌስቲቫል ወቅት በዳይሬክተሩ በኩል ይፋ እንዳያደረገው፤ ሙዚየሙ የሰበሰባቸውን ቅርሶች ሙሉና ዝርዝር ታሪክ ማብራራት ይፈልጋል ተብሏል።
ይህን ተከትሎ ከኢትዮጵያ ተነጥቀው በሙዚየሙ ከተቀመጡ ጥንታዊ ቅርሶች መካከል የወርቅ ዘውድ፣ የነገሥታትና የልዑላን የሰርግ ሥነ-ሥርዓት አልባሳትን ለመመለስ ንግግር መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል።

LEAVE A REPLY