በጃን ሜዳ የሚገኘው አትክልት ተራ በአንድ ወር ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ሥራ እንዲያቆም...

በጃን ሜዳ የሚገኘው አትክልት ተራ በአንድ ወር ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ሥራ እንዲያቆም ታዘዘ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ጊዮርጊስ አካባቢ የሚገኘው አትክልት ተራ ለአመታት ከነበረበት ቦታ ተነስቶ ወደ ጃንሜዳ እንዲዛወር ቢደረግም አሁን ላይ ነጋዴዎቹ በቀጣዮቹ ሳምንታት ውስጥ ሥፍራውን እንዲለቁ መወሰኑ ተሰማ።

በታከለ ኡማ የሥልጣን ዘመን ወደ ጃንሜዳ እንዲዘዋወር የተደረገው አትክልት ተራ በወቅቱ ሥፍራው የታቦታት ማድሪያ ከመሆኑ አኳያ ከቤተክህነት እስከ ምዕመኑ ድረስ ከፍተኛ ቁጣን መቀስቀሱ አይዘነጋም።
ከጅምሩ በቆሻሻና በአትክልትና ፍራፍሬ ብስባሾች የተጥለቀለቀውና መጥፎ ጠረን የፈጠረው የጃንሜዳው አትክልት ተራ የጥምቀት በዓል መቃረቡን ተከትሎ በቀጣዮቹ አራት ሳምንታት ውስጥ ሥራ እንዲያቆምና ነጋዴዎቹም ሥፍራውን ለቀው እንዲወጡ ለሕጋዊ ነጋዴዎችና ተደራጅተው ለመሠረቱት ማኅበር የማሳወቂያ ደብዳቤ መሰጠቱን ኢትዮጵያ ነገ ማረጋገጥ ችሏል።
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተላለፈው ይህ ውሳኔ አትክልት ተራው ወደቀድሞ ቦታው እንዲመለስና ሥራውን እንዲከወን ከማዘዙ ባሻገር ነጋዴዎቹ ለወራት ሳገለገሉበት የነበረውን ጃንሜዳን አፅድተው ወይም አፀድተው እንዲወጡ ማሳሰቡን ሰምተናል።
ሰሞኑን የጥምቀት በዓል መቃረብን ተከትሎ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ስለጃንሜዳ ከፍተኛ ቅስቀሳ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲቀርብ መቆየቱ ይታወሳል።

LEAVE A REPLY