ኢትዮጵያ ከማዕድን ዘርፍ 178 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘቷን ታከለ ኡማ ገለጹ

ኢትዮጵያ ከማዕድን ዘርፍ 178 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘቷን ታከለ ኡማ ገለጹ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከማዕድን ዘርፍ ከ178 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ መገኘቱ ተሰማ።

ባለፉት ሦስት ወራት የተለያዩ ማዕድናትን በማምረትና ወደ ውጭ ሀገር ገበያ በማቅረብ ከ178ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ እንደተገኘም ታውቋል።
ወደ ውጭ ተልከው የውጭ ምንዘሬ ካስገኙት ማዕድናት መካከል ፤ ወርቅ፣ታንታለም፣ ኳርትዝ፣ ኢመራልድ፣ ሳፓየር እና እምነበረድ ተጠቃሾች ናቸው ፡፡
 የማዕድን ሚኒስቴርን የሩብ ዓመት አፈጻጸም በተመለከተ በሰጠው መግለጫ  ላይ መግለጫውን የሰጡት የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ፤ የተመዘገበው የሥራ ውጤት በስኬት እንደሚመዘገብ አረጋግጠዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ወርቅን በተመለከተ በባህላዊ መንገድ ከሚያቀርቡ አቅራቢዎች 2ሺኅ 241 ኪ.ግ ወርቅ ለውጭ ገበያ መቅረቡን ለማወቅ ተችሏል።
አስቀድሞ በእቅድነት ተይዞ የነበረው 251 ኪ.ግ ወርቅ ለውጭ ለማቅረብ የነበረ ቢሆንም፤ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በኩል የተደረገው የወርቅ ማሻሻያ ዋጋ  የወርቅ አቅራቢዎችን መሳቡን ተከትሎ ከታቀደው በ298 ነጥብ 9 በላይ ወርቅ ለውጭ ገበያ እንደቀረበ ተሰምቷል።

LEAVE A REPLY