የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠ/ሚ/ር ዐቢይ በተገኙበት በብሔራዊ መግባባት ላይ ያተኮረ ውይይት አደረጉ

የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠ/ሚ/ር ዐቢይ በተገኙበት በብሔራዊ መግባባት ላይ ያተኮረ ውይይት አደረጉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ ህጋዊ ምዝገባ አድርገው ለቀጣዮ ምርጫ የሚፎካከሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በብሄራዊ መግባባት ላይ ያተኮረ ምክክር እያደረጉ ናቸው።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ብሄራዊ መግባባት ላይ ያተኮረ የምክክር እያካሄዱ ሲሆን ፤ በመድረኩ ላይም ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ እና የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችም መገኘታቸው ታውቋል።
በውይይት መድረኩ ሀገራዊ መግባባት እንዲፈጠር፣ መንግሥት እና ተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች ለሀገር አንድነትና ብሄራዊ መግባባት ሊሠሩ  እንደሚገባ ነው የተገለጸው።
በዚህ ወቅት በሀገሪቱ የተለያዩ ችግሮች እየተፈጠረ መሆኑ በመድረኩ የተነሳ ሲሆን፤ ሆኖም በግልፅ እንደሚታየው ችግሮችን ለመቅረፍ ከመፈራረጅ በመውጣት ለሀገር አንድነት ሊሠራ እንደሚገባም ተነግሯል።
ያለሰላም ምንም ማድረግ ስለማይቻል የሕዝብን ደህንነት ለማስጠበቅ መንግሥት የህግ የበላይነትን ሊያስከብር እንደሚገባ ያነሱት የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ በኅብረተሰቡ ዘንድ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት መንግስት ከሕዝብ ጋር ተቀራርቦ መነጋገር እንዳለበትም ተገልጿል።
ዛሬ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክክር ባደረጉበት መድረኩ ላይ የሀገሪቱ የፓለቲካ ሂደት የሚያመላክቱ ጥናታዊ ጽሑፎች እንደቀረቡም ተገልጿል።

LEAVE A REPLY