በጎንደር የተለያዮ አካባቢዎች የወባ ሕሙማን ቁጥር መጨመሩን ነዋሪዎች ገለጹ

በጎንደር የተለያዮ አካባቢዎች የወባ ሕሙማን ቁጥር መጨመሩን ነዋሪዎች ገለጹ

Macro Photo of Yellow Fever, Malaria, Dengue or Zika Virus Infected Mosquito Insect Macro on Yellow Background

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በምዕራብ ጎንደር ዞን የገንደ ውሃ ከተማ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት  የወባ ህሙማን ቁጥር በአሳሳቢ ሁኔታ መጨመሩን ነዋሪዎች ገለጹ።

በአካባቢው የወባ በሽተኛ ቁጥር ጨምሯል፤ ሁሌም በዚህ ወቅት የወባ በሽተኞች ቁጥር ይጨምራል። አሁን ግን ከበፊቱ እየጨመረ መሆኑን እያየን ነው” ያሉት ሀብታሙ አያሌው የተባሉ ነዋሪ፤ ያለው ሁኔታ አስጊ እንደሆነባቸው ለቢቢሲ አስረድተዋል።
” ዘንድሮ ኬሚካልም ሆነ የአጎበር ስርጭት ለሕብረተሰቡ ተካሂዷል። የተለየ የሚያደርገው የዝናቡ መጠን ጨምሯል። ከፍተኛ ዝናብም ነበር፤ ይህ ደግሞ ለወባ መጨመር ምክንያት ነው” የሚሉት ነዋሪው፤ በአካባቢው በወባ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ቢጨምርም እስካሁን በዚህ ምክንያት ሕይወቱ ያለፈ ሰው እንደሌለም ተናግረዋል።
በአካባቢያቸው ከነሀሴ ወር ጀምሮ በወባ የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ያረጋገጡት በመተማ ወረዳ ጤና ጥበቃ የወባ ኦፊሰር የሺሃረግ አያናው በበኩላቸው፤ ካለፉት አምስት ዓመታት አንጻር በአካባቢው ከፍተኛ የሚባል ለውጥ አለመኖሩንና ባለፉት ጥቂት ወራት ግን ቁጥሩ ማሻቀቡን አምነዋል።
በተለይም በአሁኑ ጊዜ ከሳምንት ሳምንት የተጠቂዎች ቁጥሩ እየጨመረ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎችም ከፍተኛ ቁጥር መመዝገቡን የተናገሩት ሓላፊዋ፤በአካባቢው ያሉ የቀን ሠራተኞችን ጨምሮ ብዙዎቹ አዲስ የወባ የተጠቁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY