ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሀሳብ ባለቤትነት እውን ሊሆን እንቅስቃሴው የተጀመረው ገበታ ለሀገር የጎርጎራ ፕሮጀክት መሳተፍ የፈለጉ ባለሀብቶች፣ ከ80 እስከ 300 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የፕሮጀክት ሀሳብ እያቀረቡ መሆኑን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ገለፀ።
ፕሮጀክቱ ይፋ ከሆነበት ጊዜ አንስቶ ከ100 በላይ ባለሀብቶች ጥያቄ ማቅረባቸውን የተናገሩት የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ሓላፊ አቶ ዮሐንስ አማረ፤ እነዚህ ባለሀብቶች ከ80 እስከ 300 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የፕሮጀክት ሀሳብ ይዘው ግንባታውን ለማገዝ ጥያቄ እንዳቀረቡ ገልፀዋል።
በጎርጎራ ሀገራዊ ፕሮጀክት የሚሳፈተፉ ባለሀብቶች የአምራች ኢንዱትሪ፣ የቱሪዝም ኢንቨስትመንት፣ የአትክልት እና ፍራፍሬ፣ የእንስስት እርባታ፣ የዓሳ ሀብት ልማት እና የግብርና ምርቶች ማቀነባበር ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው ነው የተሰማው።
በመላ ሀገሪቱ ከሚደረገው እንቀስቃሴ ባሻገር ከአካባቢው ማኅበረሰብ ከፍተኛ ድጋፍ ያገኘውን የገበታ ለሀገር የጎርጎራ ፕሮጀክት በያዝነው ጥቅምት ወር ይጀመራል።