የኦን ላይን ፓስፖርት የመስጠት አገልግሎት ነገ ይጀምራል ተባለ

የኦን ላይን ፓስፖርት የመስጠት አገልግሎት ነገ ይጀምራል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ ከነገ ጀምሮ የፓስፖርት አገልግሎት በኦን ላይን መሰጠት ይጀምራል ተባለ።

በኢሜግሬሽን፣ ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ተሬሳ፤  በኦን ላይን አማካኝነት የፓስፖርት አገልግሎት  ከነገ ጥቅምት 10 ቀን 2013 ዓ/ም  ጀምሮ  መስጠት እንደሚጀምር አረጋግጠዋል።
ኤጀንሲው ከዚህ በፊት ፓስፖርት እና ሌሎች ተያያዥ አገልግሎቶችን በኢንተርኔት አማካኝነት በኦንላየን እንደሚሰጥ አስታውቆ የነበረ መሆኑን ኢትዮጵያ ነገ በወቅቱ መዘገቡ ይታወሳል።
 ከጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ በኦን ላይን የቪዛ ማራዘም እና ጊዜያዊ የመኖሪያ ፍቃድ የመስጠት አገልግሎት የተጀመረ ሲሆን፤ የፓስፖርት አገልግሎት በተባለው ቀን ያልተጀመረው ሌሎች የደንህንነት እና የቴክኒክ ሥራዎች በታሰበው ጊዜ ባለመጠናቀቃቸው መሆኑን ሓላፊው ገልፀዋል።
በመሆኑም ተገልጋዮች በኦንላይን www.Evisa.com ላይ በመግባት ቪዛ ማራዘምና ጊዜያዊ የመኖሪያ ፍቃድን የመሳሰሉ አገልግሎቶችን ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፤ በአዲስ አበባ የሚሰጠው አጠቃላይ መደበኛ የፓስፖርት አገልግሎት ህዳር 1 ቀን እንደሚጀምርም ለማወቅ ተችሏል።

LEAVE A REPLY