መንግሥት ከዚህ በኋላ የኢንዱስትሪያል ፓርክ ግንባታ እንደማያካሂድ ይፋ አደረገ

መንግሥት ከዚህ በኋላ የኢንዱስትሪያል ፓርክ ግንባታ እንደማያካሂድ ይፋ አደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከእንግዲህ በኋላ መንግሥት የኢንዱስትሪያል ፓርክ ግንባታ እንደማይገነባ ተነገረ።

እንደ መግለጫው ከሆነ በመንግሥት ሙሉ በጀት የሚገነባው ወይም እየተገነባ ያለው የሰመራ ኢንዱስትሪያል ፓርክ የመጨረሻው ፕሮጀክት ይሆናል።

በመሆኑም ከዚህ የመጨረሻ ከሆነዉ የሰመራ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ግንባታ በኃላ፤ መንግሥታዊ የሆኑ ኢንዱስትሪያል ፓርኮች ግንባታን ፌደራል መንግሥቱ የሚያቆም ቢሆንም ተጨማሪ የኢንዱስትሪ ፓርኮች በግል ባለሀብቶች እንዲገነቡ እቅድ ተይዟል ነው የተባለው።
በተለያዮ የሀገሪቱ ክፍሎች የተቋቋሙትን ኢንዱስትሪያል ፓርኮችን ግንባታ ሲያካሂድ የቆየው የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ፤ ኮሚሽኑ ከአሁን በኋላ የግል ባለሀብቶች ወደ ኢንዱስትሪያል ፓርክ እንዲገቡ ማገዝ ላይ ብቻ ያተኩራል ብለዋል።

LEAVE A REPLY