ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘበች ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር አንስቶ በቫይረሱ መሞታቸው ከተነገረው ሰዎች መሀል ከአንድ ሦስተኛ የሚልቁት ኤች አይ ቪ/ ኤድስ ህሙማን የነበሩ መሆናቸው ተነገረ።
የጤና ሚኒስቴርን ጨምሮ ብሔራዊ ኤች አይ ቪ/ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽሕፈት ቤት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ለኮሮና የመጋለጥ እድላቸው የሰፋ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ሲመክር መቆየቱ አይዘነጋም።
እስካሁን በተሰበሰቡ መረጃዎች በኮቪድ 19 ምክንያት ሕይወታቸው ካለፈ ዜጎች መካከል 28 በመቶው (ከአንድ ሦስተኛው የሚልቁት) የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ሕሙማን እንደሆኑ የፌዴራል ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠር ጽሕፈት ቤት አረጋግጧል።
ይህ የሆነው ሕሙማኑ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት መድኃኒታቸውን በማቋረጣቸው መሆኑን የገለፁት የጽሕፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጽጌረዳ ክፍሌ፤ መገናኛ ብዙኃን አብዛኛውን ጊዜያቸውን ለኮቪድ -19 መስጠታቸው ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እንዲዘነጋ ምክንያት እንደሆነም ተናግረዋል።