በአዳማ ከተማ የሀዊ ሆቴል ህንፃ ተደርምሶ አራት የቀን ሠራተኞች ለሞት ተዳረጉ

በአዳማ ከተማ የሀዊ ሆቴል ህንፃ ተደርምሶ አራት የቀን ሠራተኞች ለሞት ተዳረጉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ዛሬ በአዳማ ከተማ  አንድ ህንጻ ተደርምሶ ባደረሰው አደጋ የአራት ሰው ህይወት ማለፉን  የከተማው አስተዳር ፖሊስ ገለፀ።

የአዳማ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ፤ አደጋው የደረሰው በአዳማ ደምበላ ክፍለ ከተማ ኢሬቻ ቀበሌ ውስጥ እንደሆነ ተናግረዋል።
በልዮ ስሙ ኮ/ል ደጀኔ ስሜ ትምህርት ቤት አቅራቢያ ያለው ሀዊ ሆቴል በመደርመሱ ነው ይህ ድንገተኛ  አደጋ ሊደርስ እንደቻለ ተሰምቷል።
ሆቴሉን በአዲስ ህንፃ ለመተካት በማሰብ የግንባታ ሠራተኞች አሮጌውን እያፈረሱ ባሉት ሁኔታ የቀን ሠራተኞች ላይ በደረሰው አደጋ ከመካከላቸው የአራት ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ አልፏል።
በአደጋው ሁለት ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ወደ አዳማ ሪፌራል ሆስፒታል ተወስደው በአሁኑ ወቅት የሕክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን የተናገሩት ኢንስፔክተሯ፤ የአደጋው መንስዔ የጥንቃቄ ጉድለት መሆኑንም ገልፀዋል።

LEAVE A REPLY