ኢትዮጵያ ነገ ዜና || 13 ናይጄሪያውያንና አንድ ብራዚላዊት አደንዛዥ ዕጽ ሲያዘዋውሩ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።
ዕፅ አዘዋዋሪዎቹ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት በቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን መሆኑን ፖሊስ ኮሚሽኑ ይፋ አድርጓል።
የፌደራል ፖሊስ ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ 24 የአደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን፣ 39 ኪሎ ግራም ኮኬይንና 36 ኪሎ ግራም የሚመዝን ካናቢስ (ዕፀ-ፋርስ) መያዙን ገልጿል።
በትናንትናው እለት (ጥቅምት 9፣ 2013 ዓ.ም) መነሻቸውን በቦሌ ዓለም ዐቀፍ አየር ማረፊያ፣ መዳረሻቸውን ላቲን አሜሪካ፣ ሳኦፖሎ ከተማና የተለያዩ ሀገራት በማድረግ በአውሮፕላን ሲጓዙ የነበሩት ተጠርጣሪዎችን ከአደንዛዥ ዕፆቹ ጋር በፌደራል ፖሊሶች እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ኮሚሽኑ በድኅረ ገጹ ላይ አስነብቧልደ
የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎቹ የያዙዋቸውን ዕጾች በውስጣዊና ውጫዊ የሻንጣ አካል ደብቀው እንደነበር የጠቆመው መግለጫ፤ በተጨማሪም ግለሰቦቹ በሆዳቸው በመዋጥ ፣ እንዲሁም የጡት መያዣና የተለያዩ የማዘዋወሪያ ዘዴዎችን በመጠቀም ለማሳለፍ ሙከራ ማድረጋቸውን አረጋግጧል።
በትናትናው እለት የተያዙት 13 ናይጄሪያውያንና አንዲት ብራዚላዊት ተጠርጣሪዎች 14 ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝን ኮኬይን ነው ለማሳለፍ ሙከራ ያደረጉት።