በአዲስ አበባ የሚታየውን የጤፍ ዋጋ ንረት ለማረጋጋት ለኹለተኛ ጊዜ የጨረታ ሰነድ ተዘጋጀ

በአዲስ አበባ የሚታየውን የጤፍ ዋጋ ንረት ለማረጋጋት ለኹለተኛ ጊዜ የጨረታ ሰነድ ተዘጋጀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአዲስ አበባ ሕብረት ሥራ  ኤጀንሲ ዕለት ከዕለት እየጨመረ የመጣውን የጤፍ ዋጋ ንረት ለማረጋጋት ለኹለተኛ ጊዜ የጨረታ ሰነድ እያዘጋጀሁ ነው አለ።

በግልፅ ከሚታየው ከአቅርቦትና ፍላጎት አለመመጣጠን ጋር ተያይዞ፣ ከዛም አለፍ ሲል ሆነ ብለው የዋጋ ንረት በሚፈጥሩ ኃይሎች በሚፈጠር ችግር ምክንያት ከአሁኑ በተለይ በመዲናዋ አዲስ አበባ የዋጋ ንረቶች እየታየ ነው።
በአዲስ አበባ የአንበጣ መንጋ በተለያዮ የሃገሪቱ አካባቢዎች በሰብል ላይ ጉዳት አድርሷል የሚለውን መረጃ ተከትሎ፤ በአንዳንድ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት ቢታይም በተለይ ጤፍ ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን የአዲስ አበባ ሕብረት ሥራ ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ሲሳይ አረጋ ተናግረዋል።
ቀደም ባሉት ጊዜያት በፈሳሽ የምግብ ዘይትና ሽንኩርት እጥረትና የዋጋ ንረት ወቅት ኤጀንሲው ለማስተካከል ጥረት እንዳደረገው ሁሉ፣ አሁንም በዐሥሩም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የሕብረት ሥራ ማኅበራትና የሸማቾች ሱቅ የሚዳረስ የጤፍ እህል ለማቅረብ እቅድ መያዙ ነው የተነገረው።

LEAVE A REPLY