ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ባለፉት ሦስት ወራት የውጪ ንግድ ለማበረታት በተከናወኑ ተግባራት ከውጪ ንግድ 832 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይፋ አደረገ።
ከወርቅ ውጪ ንግድ ዘርፍ 2 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱ የተገለጸ ሲሆን፣ በመግለጫው መንግሥት በበጀት ጉድለት ከብሄራዊ ባንክ ምንም ብድር እንዳልተበደረ ከመነገሩ ባሻገር፤ ባለፉት 3 ወራት ግን በመንግሥት ግምጃ ሰነድ ሽያጭ በመሸፈኑ ከብሔራዊ ባንክ እንዳልተበደረ ተገልጿል፡፡
ከብሄራዊ ባንክ ውጪ ያሉ አማራጮችን መንግሥት በመጠቀም ከመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ ከ33 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ አግኝቷል ነው የተባለው።
በተመሳሳይ ባንኩ ከሞኒተሪንግ ፖሊሲ ባለፉት 3 ወራት በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን የጠቆሙት ዶ/ር ይናገር በኢኮኖሚ ውስጥ የሚንቀሳቀሰው የገንዘብ መጠን ላይ አበረታች ሥራዎች መከናወናቸውንም አስረድተዋል።