ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ ኮቪድ 19 በሥርዓተ ምግብ እና በሕክምና ላይ የነበሩ ህሙማን የነበራቸውን የጤና ሥርዓት በተመለከተ ሀገር አቀፍ ጥናት ሊካሄድ መሆኑ ተነገረ።
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስቴር እና አጋር ተቋማት ጋር በመሆን የኮቪድ 19 ሀገራዊ ጥናት ማሰናዳቱንም እወቁልኝ ብሏል።
የኮሮና ቫይረስ የሚፈጥረው የተለያየ የሕመም ስሜትና ባህሪያት ከሥርዓተ ምግብ ጋር ያለውን ግንኙነት ጥናቱ እንደሚያካትት ታውቋል። ከዚህ በተጨማሪ በማገገሚያ ማዕከላት ውስጥ የነበሩ ታካሚዎች ላይ ክትትልና ጥናት በማድረግ መፍትኄ የሚያስቀምጥ እንደሆነም ከወዲሁ ተሰምቷል።
ከመላው ሀገሪቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የምርምር ማዕከላት የተወጣጡ ባለሙያዎች በጥናቱ እንደሚሳተፉበት በጥናቱ የማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገልጿል።
ለ1 ዓመት ያህል ይዘልቃል የተባለው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጥናት ለአጠቃላይ 100 ሚሊየን ብር ወጪ ይጠይቃል የተባለ ሲሆን፣ ይህም በጤና ሚኒስቴርና በሌሎች ረጂ ተቋማት ወጪው እንደሚሸፈን ነው የተነገረው።