ሱዳን ከ30 ዓመታት በኋላ ከእስራኤል ጋር ግንኙነቷን ያደሰች ሌላኛዋ ሀገር ሆነች

ሱዳን ከ30 ዓመታት በኋላ ከእስራኤል ጋር ግንኙነቷን ያደሰች ሌላኛዋ ሀገር ሆነች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ||  ሱዳን ከእስራኤል ጋር በሚኖራት ግንኙነት ዙሪያ ስምምነት ላይ መደረሱን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተናገሩ ማግስት ሱዳንም ከእስራኤል ጋር ግንኙነቷን ያደሰች ሌላኛዋ የአረብ ሊግ አባል አገር መሆን ችላለች።

ሱዳን ከ30 ዓመታት በላይ የገዙዋት ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ከሥልጣን መወገድ ተከትሎ የአሜሪካና የሱዳን ግንኙነት መሻሻሉን ገልጸዋል። ሱዳን ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል ደፋ ቀና ስትል የነበረው ከአሜሪካ አሸባሪነትን ከሚደግፉ አገራት ዝርዝር ውስጥ እንድትሰርዛት ለማድረግ መሆኑ አይዘነጋም።
በተያያዘ ዜና ከሰሞኑ ደግሞ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ እና ባህሬንም ከእስራኤል ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተ ስምምነት ላይ መድረሳቸው የሚታወስ ነው።
በተመሳሳይ እስራኤልና ባህሬን ግንኙነታቸውን ሙሉ በሙሉ ለማሻሻል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ይፋ ያደረጉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንደነበሩ አይዘነጋም።
ለበርካታ ዓመታት በርካታ የአረብ ሀገራት እስራኤልን የፍልስጥኤም ጉዳይ ከተፈታ በኋላ ግንኙነታቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸው የነበረ ቢሆንም፣ ባለፈው ወር የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል ስምንት ላይ ደርሳለች።

LEAVE A REPLY