ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ባለፈው ዓመት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሳይከናወን የቀረው የ12ኛ ክፍል ሀገር ዐቀፍ ፈተና በቀጣዮ ወር መጨረሻ የሚካሄድ መሆኑን ተከትሎ የተማሪዎች ምዝገባ በመጪው ሳምንት እንደሚጀመር ተነገረ።
የ2012 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር ዐቀፍ ፈተና (ማትሪክ) የተማሪዎች ምዝገባ ከጥቅምት 16 እስከ 30 /2013 ዓ.ም በየትምህርት ቤቶቹ እንደሚካሄድ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
የፈተና ምዝገባ ሂደቱን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማካሄድ በተዘጋጀው ሶፈትዌር Enrollment Kit ላይ ምዝገባ ለሚያከናውኑ የአይ ሲ ቲ ባለሙያዎችና የፈተና ክፍል አስተባባሪዎች በየክልል ከተሞች ስልጠና እንደተሰጠም ትምህርት ሚኒስቴር ከወዲሁ አስታውቋል።