ፕሬዚዳንት ትራምፕ የህዳሴ ግድቡን በተመለከተ ያደረጉትን ንግግር የኮሎራዶው ሴናተር ተቃወሙ

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የህዳሴ ግድቡን በተመለከተ ያደረጉትን ንግግር የኮሎራዶው ሴናተር ተቃወሙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አወዛጋቢው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የህዳሴውን ግድብ አስመልክቶ የተናገሩትን ንግግር አሜሪካዊው ሴናተር ተቃወሙ።

የኮሎራዶው ሴናተር ጄሰን ክሮው በትዊተር ገጻቸው ፤ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ግብፅ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ልታጋይ ትችላለች” የሚለው ንግግር ከእርሳቸው የማይጠበቅ እንደሆነ አስነብበዋል።
አሜሪካ ስለ ህዳሴው ግድብ አደራዳሪ እንጂ ጣልቃ መግባት የለባትም ያሉት ሴናተሩ፤ ጉዳዩ በሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲያልቅ መሥራት ያስፈልጋል ሲሉም የትራምፕን ንግግር ተችተዋል።
የትራምፕ ንግግር የግድቡን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ከግንዛቤ ያላስገባ መሆኑን ያስረዱት፤ ኢትዮጵያ የአሜሪካ የረዥም ዘመናት የልብ ወዳጅ መሆኗንም አስታውሰዋል።

LEAVE A REPLY