ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ያደረጉትን ንግግር በይፋ አወገዘ።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ የፕሬዝዳንቱ ንግግር ከአንድ መሪ የማይጠበቅ መሆኑን ጠቁመው፤ በመሆኑም ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በአንድነት እና በመቻቻል የጀመርነውን የህዳሴ ግድብ ከግብ ማድረስ ይጠበቅብናል ሲሉም መልእክት አስተላልፈዋል።
ግብፅም ብትሆን የፕሬዝዳንቱን የተሳሳተ ንግግር በመስማት ለጥፋት እንዳትነሳሳ ያሳሰቡት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ እድሪስ፤ ሀገሪቱ የራሷን እና የኢትዮጵያን ጥቅም ባስከበረ መልኩ ብቻ ልትንቀሳቀስ እንደሚገባም አሳስበዋል።
ዶናልድ ትራምፕ አርብ ምሽት በዋይት ሃውስ ለጋዜጠኞች “ኢትዮጵያ ወደ ስምምነቱ መመለስ አለባት፤ ግብጽ ብስጭት ቢገባት ልትኮነን አይገባም፤ ግድቡነ ልታፈነዳው ትችላለች” ሲሉ አስገራሚ ንግግር ማድረጋቸው አይዘነጋም።