በመንግሥት መ/ቤቶች የሚገኙ አሮጌ መኪኖች ከዚህ በኋላ በቁርጥራጭ ብረታ ብረት ስም ይሸጣሉ...

በመንግሥት መ/ቤቶች የሚገኙ አሮጌ መኪኖች ከዚህ በኋላ በቁርጥራጭ ብረታ ብረት ስም ይሸጣሉ ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በየመንግሥት መሥሪያ ቤቱ አገልግለው በየጥጋጥጉ የቆሙ መኪኖች በጨረታ ሲወገዱ አሮጌ በመሆናቸው ለአካባቢ ብክለት ምክንያት እንዳይሆኑ በሚል ከዚህ በኋላ በመኪና ስም ሳይሆን በቁርጥራጭ ብረታ ብረት ስም በሽያጭ እንደሚወገዱ ተወሰነ።

በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ አገልግሎት መስጠት ያቆሙ ተሽከርካሪዎችን በሽያጭ በማስወገድ ገንዘቡን ለመንግሥት ገቢ የሚያደርገው የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት እንደሆነም ታውቋል።
በያዝነው ዓመት ባለፉት 3 ወራት ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ የተለያዩ ንብረቶችን በሽያጭ በማስወገድ 11.2 ሚሊየን ብር ለመንግሥት ገቢ ማስገኘቱን የገለጹት የመሥሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፅዋዬ ሞላ፤ አሁን ካለው የመንግሥት ፖሊስ አንጻር ያረጁ መኪኖችን በሽያጭ በማስወገድ ተመልሰው መንገድ ላይ እንዲወጡ ማድረጉ ለአካባቢ ብክለትና በትራፊክ አደጋ መጨመር ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ ብለዋል።
ይህንን ተከትሎ በየመሥሪያ ቤቱ በየጥጋ ጥጉ ቆመው ፀሐይና ዝናብ የተፈራረቀባቸውን መኪኖች ለተሽከርካሪነት ከመሸጥ ይልቅ በቁርጥራጭ ብረትነት ለማስወገድ ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ጋር በጋራ መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን ወ/ሮ ፅዋዬ ገልፀዋል።
በቁርጥራጭ ብረትነት የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች በቀጥታ ለብረት አቅላጭ ፋብሪካዎች የሚቀርቡ ሲሆን፣
በሌላ በኩል የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ባለፉት 3 ወራት ከዓለም ባንክ በተገኘ እርዳታ 80 ሺኅ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዥ ፈፅሞ ለገንዘብ ሚኒስቴር ማስረከቡን አስታውቋል።

LEAVE A REPLY