ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አሠልጣኝ ተመስገን ዳና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ወንዶች ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን አሠልጣኝ ሆነው መሾማቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
አሠልጣኙ በዛሬው ዕለት የአንድ ዓመት ውል ኮንትራት ቀርቦላቸው ፊርማቸውን ያኖሩ ሲሆን፣ በሴካፋ ተፎካካሪ መሆን የሚችልና ውጤታማ የሆነ ቡድን እንዲሠሩ ግዴታ እንደተጣለባቸውና እርሳቸውም ይሄንን እንደተቀበሉ ተገልጿል።
አሠልጣኝ ተመስገን ከዚህ ቀደም ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኑ በሴካፋ የፍጻሜ ተፋላሚ ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
በቅርቡ አሠልጣኝ ውበቱ አባተን የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሠልጣኝ አድርጎ የሾመው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በተከታይ በሴት ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን (ሉሲዎቹ) ላይም አዲስ የአሠልጣኝ ሹም ሽር ያካሂዳል ተብሎ ተገምቷል።