ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአመራር ብልሹነት እና ሙስና ምክንያት ከ100 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሳይሰበስብ መቅረቱን የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (የቀድሞው ጅንአድ) አስታወቀ።
ድርጅቱ የሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀምን ድርጅቱ በገመገመበት መድረክ ላይ የተገኙት የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተካ ገብረየስ ፤ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ከተቋሙ መገኘት ያለበትን አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችል ሪፎርም እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
የተቋሙ ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሮ የሺእመቤት ነጋሽ ባቀረቡት ሪፖርት፤ በሰው ሀይል ብቃት ማነስና በአመራር ብልሹነት በተፈፀመ ሙስና፣ ተቋሙ ከ100 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰብ የነበረበትን ገቢ ሳይሰበስብ እንደቀረ ጠቁመው፤ ከዚህም በተጨማሪ የጥራት ጉድለት ባለባቸው እቃዎች ግዢ ምክንያት ከ400 ሚሊየን ብር በላይ ሀብት ሳይሸጥ በመጋዘን ውስጥ ተከማችቶ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ተቋሙ ለደንበኞች በሚሰጠው አገልግሎት ላይ ባለው ችግር ምክንያት ተቋሙ ተአማኒነት እያጣ መሆኑን ተከትሎ፣
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ድርጅት ለዚህ ኪሳራ ያበቁትን ሥድሥት ከፍተኛ አመራሮች ከሥራ ማሰናበቱ በሩብ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርቱ ላይ ተገልጿል።